የይለፍ ሰነድ


ከሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ምክንያት ፓስፖርት በእጃቸው ላይ ሳይኖር ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲያስችላቸው ብቻ በኤጀንሲው ተዘጋጅቶ የሚሰጥ የጉዞ ሰነድ ነው፡፡ በዚህ ሰነድ ተመልሶ ከሀገር ለመውጣት አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ሰነዱ ሶስት ወርና ከዚያ በታች የፀና የአገልግሎት ጊዜ አለው፡፡
=>  ፓስፖርት ለሌለው ከውጭ ወደ ሃገሩ ለሚመለስ ኢትዮጵያዊ ይሰጣል፡፡
=> በተለያዩ ምክንያት ከሃገር ወጥተው ፖስፓርት ለጠፋባቸው ወደ ሃገር መመለስ ለሚጠይቁ ኢትዮጵያውያን ለ1 ጊዜ ወደ ሀገር ለመግባት የሚሰጥ ሰነድ ነው ፖስፓርታቸው  ለመጥፋቱ ለሚሲዮኑ በጽሁፍ         ጥያቄ ሲያቀርቡ ተጣርቶ ይሰጣል፡፡