=> ልደት ለማስመዝገብ የህፃኑ ወላጆች መኖር አለባቸው፡፡
የልደት አስመዝጋቢዎች :-
=> የህፃኑ ወላጆች በህይወት ካሉ አባት እና እናት ሁለቱ ከሁለቱ አንዱ
=> በህይወት የሌሉ እንደሆነ በህይወት ያለው እናት ከሆንች እናት አባት ከሆነ አባት
=> ሁለቱም ወላጆች በህይወት የሌሉ ከሆነ የህፃኑ አሳዳሪ ወይም ህፃኑን በመንከባከብ ላይ ያለ አካል
=> ተጥሎ የተገኘ ህፃን ከሆነ ፓሊስ ወይም አግባብነት ያለው አካል ይሆናሉ፡፡
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
=> አስመዝጋቢው ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ
የሆነ ውጭ ዜግነት መታወቂያ ማቅረብ አለበት፡፡
=> ልደቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ አስመዝጋቢው ከጤና ተቋም የተሰጠውን የልደት ማሳወቂያ ምስክር ወረቀት
ማቅረብ አለበት፡፡
=> የህጻኑ አሳዳሪ ወይም ሕጋዊ ሞግዚት ልደቱን ለማስመዝገብ ሲቀርብ ከፍርድ ቤት የተሰጠ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
=>ተጥሎ የተገኘ ህፃንን ለማስመዝገብ የሚመጣ ፖሊስ ወይም አግባብ ያለው የመንግስት አካል ማንነቱን የሚገልጽ ሕጋዊ
መታወቂያ ወይም ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
=> ዘግይተውና የምዝገባ ጊዜውን አሳልፈው ለሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች በእስር ወይም በህመም ወይም በመሳሰሉት የቆዩ
ከሆነ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
=> ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የኩነት ምዝገባ ደጋፊ ሰነዶች በኢትዮጵያ ኤምባሲና ቆንሲላ ጽሕፈት ቤቶች
ካልተረጋገጡ ቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
=> በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ የውጭ አገር ኤምባሲዎችና ቆንስላ
ጽሕፈት የተረጋገጡ ኩነት ለማስመዝገብ ደጋፊ ሰነዶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ካልተረጋገጡ ተቀባይነት የላቸውም፡፡