የሞት ምዝገባ

=> ከሟች ጋር አብሮ ይኖር የነበረ ሰው፣ አብሮ ይኖር የነበረ ሰው የሌለ እንደሆነ የሟች የስጋ ወይም የጋብቻ ዘመዶች፣
     እነዚህ የሌሉ እንደሆነ የቅርብ ጎረቤት ወይም ስለሟቹ መሞት የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ሟች መሞቱን ማስመዝገብ አለበት፡፡
=> ሞቱ የተከሰተው በጋራ መኖሪያ ስፍራ ከሆነ የተቋሙ ሃላፊ ሞቱን ለማስመዝግብ መቅረብ አለበት፡፡
=> በአደጋ ምክንያት ከሞቱ ሰዎችና አደጋው ከደረሰባቸው ተጎጂዎች ጋር አብሮ የነበረ ሰው ሊገኝ አለመቻሉን ካጣራ አካል
     የተሰጠ ማስረጃ ሲቀርብ ሞቱ ይመዘገባል፡፡
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

=> ሞቱ የተከሰተው በጤና ተቋም ከሆነ ከጤና ተቋም የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
=> የሟች የነዋሪነት/ብሄራዊ መታወቂያ መቅረብ አለበት፡፡
=> ሞቱን የሚያስመዘግበው ፖሊስ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ/ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
=> ሞቱ የሚመዘገበው በግለሰቡ መጥፋት ውሳኔ ምክንያት ከሆነ የፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ መቅረብ አለበት፡፡
=> የጊዜ ገደቡ ባለፈ ምዝገባ ለሚመዘገብ ሞት ስለሞቱ መከሰት የሚገልፅ የተረጋገጠ የፅሑፍ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
=> ማስረጃው የሚቀርበው ከእድር፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከመስጂድ እና ከመሳሰሉት ይሆናል፡፡
=> ዘግይተውና የምዝገባ ጊዜውን አሳልፈው ለሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች በእስር ወይም በህመም ወይም በመሳሰሉት የቆዩ
     ከሆነ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው