የፍቺ ምዝገባ

=> ፍቺው በተፋቺዎቹ የጋራ ወይም ከተፋቺዎች በአንዱ መደበኛ መኖሪያ ቦታ በሚገኝ ፍርድ ቤት የተፈጸመ መሆን አለበት፣
=> የፍቺ ምዝገባ በአዋጁ አንቀጽ 36 ስር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁለቱ ተፋቺዎች አብሮ ይኖሩበት በነበረው
      መደበኛ መኖሪያ ቦታ በሚገኝ የአስተዳደር ጽህፈት ቤት መሆን አለበት፣
=> የፍቺ አስመዝጋቢ ሆነው የሚቀርቡት ተፋቺዎች በጋራ ወይም ከተፋቺዎች አንዱ ወይም የተፋቺዎች ህጋዊ ወኪል
      መሆን አለበት፣
ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

=> ፍቺው በፍርድ ቤት የተከናወነ መሆኑን የሚገልፅ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ መቅረብ አለበት፡፡
=> ተፋቺዎች ፍቺውን ለማስመዝገብ ሲመጡ ጊዜው ያላለፈበት የነዋሪነት ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት
    ማቅረብ አለባቸው፣
=> ፍቺው የሚመዘገበው በወኪል ከሆነ ልዩ ውክልና ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
=> ቀደም ሲል የጋብቻ ምስክር ወረቀት የተሰጠ እንደሆነ የጋብቻ ምስክር ወረቀት መመለስ አለበት፣
=> ዘግይተውና ጊዜ አሳልፈው ለሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች በእስር ወይም በህመም ወይም በመሳሰሉት የቆዩ ከሆነ ከሚመለከተው
    አካል ማስረጃ
=> አለበት፣ ዘግይተውና ጊዜ አሳልፈው ለሚቀርቡ ተመዝጋቢዎች በእስር ወይም በህመም ወይም በመሳሰሉት የቆዩ
    ከሆነ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ