አስቸኳይ የጉዞ ሰነድ


 በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገራችን ገብተው ሀገር ውስጥ እያሉ የጉዞ ሰነዳቸው ጠፍቶባቸው የሀገራቸውን ፓስፖርት በተለያየ ምክንያት ማግኘት ያልቻሉ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው     እንዲመለሱ ለማስቻል በኤጀንሲው ተዘጋጅቶ የሚሰጥ የጉዞ ሰነድ ዓይነት ነው፡፡ የአገልግሎት ጊዜው በጣም አጭር የሆነና ወደ ሌሎች አገራት የሚወጡበት ሲሆን ተመልሰው ወደ     ኢትዮጵያ ሊመጡበት እንዳይችሉ ተደርጎ የሚሰጥ ነው፡፡ አስቸኳይ የጉዞ ሠነድ የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው ፡፡