አገልግሎቶች

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለኢትዮጵያውያን እና ለውጪ ሀገር ዜጎች እነዚህን አገልግሎቶች ይሰጣልNews | ዜና

የመጨረሻ ማሳሰቢያ

የኢፌዴሪ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያየ መንገድ ገብተው የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገር ዜጎችን የመመዝገብና የመቆጣጠር ስልጣን በአዋጅ 354/1995 በተሰጠው መሰረት ከሐምሌ 11 እስከ 25/2014 ድረስ፡-  በተለያዩ የቪዛ ዓይነት ወደ ኢትዮጵያ የገቡና ቪዛቸው የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤  የመኖሪያ ፈቃዳቸው የሚፀናበት ጊዜ ያለፈበት፤  ምንም አይነት ቪዛም ሆነ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው፤  በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት ወይም የጥገኝነት ጠያቂ ዕውቅና አግኝተው በከተማ ስደተኝነት ለመኖር የተፈቀደላቸው ወይም ያለፈቃድ ከተለያየ የስደተኛ ጣቢያ በመምጣት የሚኖሩ የዉጭ ዜጐችን መመዝገቡ ይታወቃል። ሆኖም ግን በተለያየ ምክኒያት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ዉስጥ ያልተመዘገቡ በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ የውጭ ዜጎች እዲመዘገቡ እና በህግ አግባብ እዲንቀሳቀሱ እድል ለመስጠት ሲባል ከነሐሴ 3-10/2014ዓ.ም ድረስ ለመጨረሻ ጊዜ ምዝገባ ስለሚያከሄድ፤ የሚመለከታችሁ የዉጭ አገር ዜጎች ዘውትር በስራ ሰዓት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በሁሉም ስራ ቀናት ማንነታችሁን የሚገልፅ ሕጋዊ ሠነድ /ፓስፖርት፣ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የስደተኛ መታወቂያ ወይም የምዝገባ ማረጋገጫ ሰነድ ፣ የጉዞ እና/ወይም ሌሎች ተያያዥ ሠነዶችን/ ይዛችሁ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ • በአዲስ አበባ ከተማ፡- በሁሉም የወረዳ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ/ቤቶች እና ፒያሳ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ • በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች፡- ገላን፣ ዱከም፣ ለገጣፎ፣ ሱሉልታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ እና ሰበታ እንዲሁም ቢሾፍቱ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ፅ/ቤቶች ናቸው፣ ከላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ባልተመዘገቡ የውጭ አገር ዜጎች ላይ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ ማሳሰቢያ፡- በህግ አግባ በኢትዮጵያ ዉስጥ እንዲኖሩ ያልተፈቀደላቸውን የውጭ አገር ዜጐችን በመቅጠር የምታሰሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች፣ በማከራየት ወይም በጥገኝነት የምታኖሩ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ መመዝገባቸውን እና የምዝገባ ማረጋገጫ መውስዳቸውን እንድታረጋግጡ እያሳሰብን፤ ይህን በማይፈፅሙ ላይ የህግ ተጠያቂነት እንደሚያስከትል እናሳውቃለን። ለበለጠ መረጃ ድረገፃችንን ይጎብኙ፡- www.invea.gov.et. የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ


መጠሪያችን

በኢትዮጵያ የብልጽግና ሪፎርም የለውጥ ስራዎች በተለያዩ ተቋማት የነበሩ ስራዎችን በማሰተሳሰር እንደ አዲስ የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ በዚህም የኢፌዲሪ የኢምግሬሽንና ዜግነትና አገልግሎት በመባል ይጠራል፡፡


አድራሻችን

አድራሻ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ኢሜል

fdreimmigrationvea@gmail.com

ስልክ

8133