የመኖሪያ ፊቃድ


1. ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ 
=> ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጣቸው የማይችል የውጭ አገር ዜጎች የሚሰጥ መታወቂያ ነው፡፡
ይህ የፈቃድ ዓይነት እስከ አንድ አመት ድረስ የሚያገልግልና የሚታደስ ነው፡፡          
ዲፕሎማቲክ ስራ እያከናወኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ የውጭ ዜጎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲፕሎማቲክ ደረጃ የያዘ የመኖሪያ ፍቃድ ይሰጣል፡፡ ይህም እስከ ሁለት አመት የፀና የአገልግሎት ጊዜ ያለው ሲሆን ጊዜው ሲደርስ በውጭ ሚ.ኒስቴር የሚታደስ የሚታደስ ነው።
2. ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ
=>  በመኖሪያ ቪዛ ወደ ሀገር ለመኖር ለሚገቡ እና ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲኖሩ ለተፈቀደላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ለአምስት ዓመት እና እንዳስፈላጊነቱ በሚጨመር ጊዜ        የሚያገለግል መታወቂያ ነው፡፡ከዚህም ሌላ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት በተሰማሩና ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ትስስር ላላቸው የውጭ ዜጎች ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጣል፡፡

                                                                                                    ለበለጠ መረጃ እና ለተለያዩ የመኖሪያ ፈቃድ እዚህ ያመልክቱ